የሕግ ማውጣት፣ጥናትና ምክር ዳይሬክቶሬት

የህግ ማውጣት፣ ጥናት፣ ምክርና ዶክመንተሸን ዳይሬክቶሬት ዋናዋና እና ተከታታይ ተግባራት

ቤቱ ፀድቀው የሚወጡ ህጎች ግልጽ፣ ተፈፃሚና ጥራት ያላቸው የህብረተሰቡን ፍላጎትና ጥቅም የሚያስጠብቁ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
ህጎች ከሕገ መንግስቱና ከሌሎች ህጎች ጋር የማይጋጩ እንዲሁም ከመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን የማረጋገጥ ሥራ ይሠራል፡፡
ህጎች የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችና ነፃነቶች የሚያስጠብቁ፣ የፆታ እኩልነትን የሚያረጋግጡ፣ ልማትና መልካም አስተዳደርን የሚያሰፍኑ መሆናቸው ይፈተሻል፡፡
ረቂቆች በዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች ተመርምረው ሙያዊ አስተያየት ተሰጥቶባቸው ለቋሚ ኮሚቴዎች እንዲቀርቡ ይደረጋል፡፡
ይውጣልኝ ጥያቄዎች በአሠራርና ሥነ ምግባር ደንቡ መሠረት ከጉባኤ አስራ አምስት ቀን በፊት ለምክር ቤቱ እንዲቀርቡ ይደረጋል፡፡
ህጎች በአሠራርና ሥነ ምግባር ደንቡ መሠረት በምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎችና የሥራ ሂደቱ በባለሙያዎች በአግባቡ እንዲመረመሩ ይደረጋል፡፡
አወጣጥ ሂደቱን ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ በምክር ቤቱ ጉባኤ በረቂቅ ህጎች ላይ የሚሰጡ ማስተካከያዎችና አስተያየቶችን የማካተት ሥራ በሌላ ተቋም (ፍትህ ቢሮ) የሚደረገውን በማስቀረት በምክር ቤቱ ከፍተኛ የህግ ባለሙያዎች እንዲከናወን ማድረግ ይቻላል፡፡
አሠራር ጋር የሌሎች ሀገሮች ልምድን በመቀመር በጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል
ቤቱን አሠራር የሚያቀላጥፉ ደንቦች መመሪያዎችና የአሠራር ማንዋሎች እንዲወጡ ይደረጋል
ህጎች በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋ፣ በሶፍትና በሀርድ ኮፒ ተሟልተው እንዲቀርቡ ይደረጋል
አወጣጥ ሂደት አሳታፊ አሰራሮችን በመዘርጋት ተግባራዊ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
ቀርበው የፀደቁ የህግ ረቂቆች ላይ የተሰጡ ማስተካከያዎችና አስተያየቶችን በዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች በማካተት ለህትመት የሚላኩበት አሰራር በመዘርጋት ተግባራዊ እንዲሆን ይደረጋል
አወጣጥ ሂደት የህዝብ ውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት ለህግ ጥራትና ተፈፃሚነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
ቤቱ ያሳለፋቸው ውሳኔዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች ለሚመለከታቸው አካላት በወቅቱ እንዲደርስ ይደረጋል፡፡
የሚቀርቡ ረቂቅ አዋጆች የአማርኛና የእንግሊዝኛ ቅጂዎች ተመሳሳይና ልዩነት የሌላቸው መሆኑ የማረጋገጥ ሥራ ይሰራል፡፡
ህጎችን ለማሳተም የሚረዳ ተዘዋዋሪ በጀት በማስመደብ ህጎች በወቅቱ ታትመው በምክር ቤቱ እንዲሰራጩ ማድረግ ይቻላል
ቤቱ በየጊዜው የሚያወጣቸው ህጎች በደቡብ ነጋሪት ጋዜጣ በወቅቱ ታትመው እንዲወጡ ይደረጋል፣
ነጋሪት ጋዜጣ ታትመው የወጡ ህጎችን በቤተ መጽሀፍ በማስቀመጥ ለህዝብ ተደራሽ ይደረጋል
ቤቱ ደንቦችና መመሪያዎች ክፍተትን መሙላት በሚያስችል መልኩ በሥራ ክፍሉ ባለሙያዎች የሚዘጋጁ ይሆናል፡፡
የወጡ ህጎች የአፈፃፀም ክፍተቶች በሥራ ክፍሉ ባለሙያዎች በጥናት በመለየት ከመፍትሄ ሃሳብ ጋር ለሚመለከተው አካል እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡
፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በሥራ ክፍሉ ባለሙያዎች የጥናት ሥራዎች እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡
ጥናት መድረክ በማዘጋጀት በጥናት በተለዩ ችግሮችና በተቀመጠው የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ ውይይት በማድረግ ነባር ህጎች እንዲሻሉ ይደረጋል
ሕጎች ላይ የሚደረጉ ጥናቶች በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ በዕቅድና በበጀት የተደገፉ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
ክፍተቶች በህግና የተለያየ የሙያ ክህሎት ባላቸው ባለሙያዎች ቢጠኑ ክፍተቶችን በቀላሉ መለየት ያስችላል፡፡
ከማውጣት ጐን ለጐን የወጡ ህጎችን ተገልጋዮች/ ተጠቃሚዎች እንዲያውቋቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱ ክትትል ይደረጋል፡፡
ቤቱ አመራሮች፣ ጽህፈት ቤትና በየደረጃው ለሚገኙ ምክር ቤቶች ሙያዊ የህግ ምክርና ድጋፍ አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል
ሙያዊ የህግ ድጋፍና የማማከር ፍላጎት /ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንዲገኙ ይደረጋል፡፡
ሙያዊ የህግ ድጋፍና የማማከር አገልግሎቶች መረጃን መሠረት ያደረጉ በተሟላ ግንዛቤ ላይ የተመሠረቱ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
ቤቱ ውስጥ ሁሉ አቀፍ የቃለ ጉባኤ አያያዝ አገልግሎት ስርዓት እንዲዘረጋ ይደረጋል
ሂደቶች፣ ፎረሞች፣ የቋሚ ኮሚቴ ውይይቶችና የህዝብ መድረክ ቃለ ጉባኤዎች በመስኩ በሰለጠኑ ባለሙያዎች በአግባቡ እንዲያዙ ይደረጋል፡፡
ጉባኤዎች በተለያየ የቃለ ጉባኤ አያያዝ ዘዴዎች በፅሁፍ ተዘጋጅተው ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሱና በመረጃ ማዕከል ተደራጅተው እንዲቀመጡ ይደረጋል
ቃለ ጉባኤዎች በሶፍት ኮፒ ተዘጋጀተው ለምክር ቤቱ አባላት በየአድራሻቸው በኢሜል እንዲደርሳቸው ይደረጋል
አባላት በጉባኤ የሰጡዋቸው አስተያየቶችን ከቀጣይ ጉባዔ በፊት እርምት ሰጥተው እንዲልኩ በኢሜል አድራሻቸው እንዲደርሳቸው የሚያስችል ሥራ ይሰራል
ህጎች፣ ቃለ ጉባኤዎች፣ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎች በሥራ ሂደቱ በአግባቡ ተደራጅተው የሚቀመጡበት አሰራር ይፈጠራል፡፡
ቤቱ ቃለ ጉባኤዎችና ሌሎች የጉባኤ ሰነዶች ከ48 ሠዓት በፊት ለአባላት እንዲደርሱ ይደረጋል፡፡
ቤቱ የሚቀርቡ ረቂቅ ህጎች በአማርኛ እና በአንግሊዝኛ ቋንቋ ተዘጋጅቶ ከማብራሪያ ጋር እንዲቀርቡ ይደረጋል፡፡
ሂደት፣ ፎረም፣ የቋሚ ኮሚቴዎች የክትትልና ቁጥጥር እንቅስቃሴዎች፣ የህዝብ አስተያየት መድረኮች፣ ስብሰባዎችና ስልጠናዎች በሥራ ሂደቱ ባለሙያዎች በድምጽ፣ በምስልና በቪዲዮ እንዲቀረፁ ይደረጋል፡፡
ቅድመ ዝግጅት ስራዎችና የጉባዔ አዳራሽ አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲሠራ ይደረጋል
ቤት አባላት የህዝብ ውክልናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ ምቹ፣ ጽዱና የተሟላ የጉባኤ አዳራሽ አገልግሎት በሥራ ሂደቱ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡
ቤቱ ጉባኤ ሰነዶች ለእያንዳንዱ የምክር ቤት አባላት በስማቸው በተዘጋጁ ሳጥኖች ውስጥ በማስቀመጥ በቀላሉ እንዲደርሳቸው ይደረጋል
ቤቱ የሚዘጋጁ የተለያዩ ሰነዶች ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲታተሙና እንዲጠረዙ በማድረግ ለተጠቃሚዎች እንዲሰራጭ ይደረጋል
ሂደቱ መረጃዎች በኦዶቪዥዋል፣ በሀርድ ኮፒና በሶፍት ኮፒ በአንድ ማዕከል እንዲደራጁ ይደረጋል
ቤቱ ዋና ዋና ተግባራት ላይ የሚያጠነጥን ፓርላሜንታሪ ሀንድ ቡክ /Parlamentary Hand Book/ እንዲዘጋጅ ይደረጋል
ሂደቱ መረጃዎች ለህግ ማውጣት፣ ለጥናትና ምርምር ሥራ እንዲያግዙ ሆነው እንዲደራጁ ይደረጋል
ቤቱ ፀድቀው የወጡ ህጎች ተደራጅተውና በተገቢው ተጠርዘው እንዲቀመጡ ይደረጋል፡፡
ቤቱ ጉባኤዎች፣ አውደ ጥናቶች፣ ስልጠናዎችና የምክክር መድረኮች የሚቀርቡ ፅሁፎች በሥራ ሂደቱ ተደራጅተው እንዲቀመጡ ይደረጋል
የፎረም፣ የቋሚ ኮሚቴና የሥራ ሂደቶች፣ የህዝብ መድረኮች፣ የጥናት፣ የስልጠናና የመወያያ ሰነዶች የህትመት አገልግሎት ጥራቱን ጠብቆ በሥራ ሂደቱ እንዲከናወን ይደረጋል፡፡
ሂደቱ በከፍተኛ ባለሙያዎች የተደራጀ እንዲሆን ይደረጋል፣
ምልልስ የበዛባቸው አሰራሮችንና ያለክንውን የሚባክን ጊዜን በማሳጠር የአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋና ፈጣን እንዲሆን ይደረጋል
ሂደቱ አገልግሎት ጥራቱን የጠበቀና የተቀላጠፈ የተገልጋዮችን ፍላጎት የሚያረካ እንዲሆን ይደረጋል፡፡