የክትትል፣ ቁጥጥርና ሙያዊ ድጋፍ ዳይሬክቶሬት
የክትትል ቁጥጥር ሙያዊ ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቶሬቱ የሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት 1.የመንግስት አካላት እቅድና የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት መመርመር፣ ሙያዊ አስተያየት መስጠት የመንግስት አካላት አሠራር ክትትልና ቁጥጥር የህዝቡን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲከናወን የሚያስችሉ የአሰራር ሥርዓቶችን በመቅረጽ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣ ከመንግስት አካላት ለምክር ቤቱ የሚቀርቡ የሥራ እቅዶች በአዋጅ የተሰጠ ሥልጣንና ተግባራትን ማዕከል አድርገው፤ ከተቋማቱ ተግባራት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ሊያሳካ በሚችል መልኩ የታቀዱ መሆናቸውን ይመረምራል፤ ያረጋግጣል፣ ሙያዊ አስተያየት ይሰጣል፡ የመንግስት አካላት የአፈጻጸም ሪፖርት በእቅዱ መሠረት የተከናወነ መሆኑን፣ በጀት ለተመደበለት ሥራ መዋሉን፣ በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የተገኘውን ውጤት ለይቶ ያመላከተ መሆኑን ይመረምራል፤ ያረጋግጣል፣ የመንግስት አካላት የአፈጻጸም ሪፖርት ከፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አንፃር በመገምገም የአፈጻፀም ክፍተቶችን እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት ሙያዊ አስተያየት ያዘጋጃል፣ ለቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ ይሰጣል፣ የመንግስት አካላት በአካል ቀርበው በእቅድና በአፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡ ያመቻቻል፣ ለቋሚ ኮሚቴው መረጃዎችን አደራጅቶ በማቅረብ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፣ ግብረ መልስ በማዘጋጀት ያቀርባል፣ በቋሚ ኮሚቴው የተሰጡ ግብረ መልሶች ተፈፃሚ ያደረጉና ያላደረጉ የመንግስት አካላትን በመለየት ከአስተያየት ጋር ያቀርባል፤ 2. የመስክ ክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ፣ በክልሉ መንግስት ተግባራዊ በመደረግ ላይ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አተገባበር የክትትልና ቁጥጥር ሂደት ውጤታማ ለማድረግ የሚረዱ ስልቶችን በመቀየስ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣ በሥራ ላይ የዋሉ ሕጎች፣ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አተገባበር ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ የሚረዱ ሰነዶችንና ቼክ ሊስቶች ያዘጋጃል፣ በመስክ ክትትልና ቁጥጥር ወቅት ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፤ በአፈፃፀም የታዩ ክፍተቶች ሊደፈኑ የሚችሉበት ሁኔታ ቋሚ ኮሚቴውን ያማክራል፣ ሙያዊ አስተያየት ይሰጣል፣ የተጠቃለለ የመስክ ሥራ ሪፖርትና ግብረ መልስ ያዘጋጃል፣ የተሰጠ ግብዓት በማካተት ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል፣ 2. የሕዝብ አስተያየት መሰጫ መድረኮችንና የመወያያ ሠነዶችን ማዘጋጀት የሕዝቡ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በማዳመጥ ተገቢው ምላሽ እንዲያገኙ የሚረዱ ችግር ፈቺ የሆኑ ስትራቴጂያዊ አሠራሮችን በማፍለቅ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤ የሕዝብ አስተያየት መስጫ መድረኮች ለማካሄድ የሚካሄዱ የዳሰሳ ጥናቶችን በበላይነት ይመራል፣ ያስተባብራል፣ በምክር ቤቱ የሚከናወኑ የሕዝብ አስተያየት መስጫ መድረኮችን በመለየት የመወያያ ሰነዶችን ያዘጋጃል፣ የማስፈፀሚያ ዕቅዶችን በማዘጋጀት ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣ የሕዝብ አስተያየት መስጫ መድረኮችን ያስተባብራል፣ የህዝቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና አስተያየቶች፣ በሴክተር የሥራ ኃላፊዎች የተሰጡ ምላሾች እና በቋሚ ከኮሚቴው የተቀመጡ አቅጣጫዎች መሠረት ግብረ መልስ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ በሕዝብ መድረኩ የተነሱ ጉዳዮች አስመልከቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚካሄዱ መድረኮችን ያዘጋጃል/ ያመቻቻል፣ ለህዝቡ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተወሰዱ ተግባራዊ እርምጃዎች በመለየት ከሙያዊ አስተያየት ጋር ያቀርባል፣ 3. የህዝብ አቤቱታና ጥቆማዎችን በመመርመር ከውሳኔ ኃሳብ ጋር ሙያዊ አስተያየት መስጠት ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ የተመሩ የሕዝብ አቤቱታና ጥቆማዎችን ከሕገ መንግስቱና ከምክር ቤቱ የአሠራርና የሥነ ምግባር ደንብ አንፃር ተገቢነቱን ያረጋግጣል፣ የቀረበውን አቤቱታ በተመለከተ መረጃዎችን በመሰብሰብ አደራጅቶ በመተተንተን ከውሳኔ ኃሳብ ጋር ያቀርባል፣ ተጨማሪ ማጣራት ለሚያስፈልጉ ጉዳዮች ከቋሚ ኮሚቴው ጋር በመሆን በአካል ምልከታ በማድረግ መረጃዎችን በማጣራት ለውሳኔ የሚረዳ ሀሳብ ያቀርባል፤ ሕዝቡ አገልግሎቱን በምክር ቤት መሰጠቱን አውቆ እንዲገለገል የግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራዎችን ይሰራል ሕዝቡ ጥቆማና አስተያየቶችን ባለበት ቦታ ሆኖ ማቅረብ በሚችልበት ሁኔታ ጥናት በማድረግ አማራጭ ስልቶችን በመዘርጋት ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣ አማራጭ ስልቶችን በመጠቀም የሚቀርቡ የህዝብ ጥቆማዎችንና አስተያየቶችን በማጣራት ለውሳኔ የሚረዳ ሀሳብ ያቀርባል፤ 4. የአቅም ግንባታ የስልጠና ሰነድ ማዘጋጀት፣ ስልጠና መስጠት በምክር ቤቱ የሚከናወኑ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በመለየት የስልጠና ሰነዶችን፣ ማንዋሎችን ያዘጋጃል፣ ለስልጠናው የሚስፈልግ የበጀት መጠን በመለየት የበጀት ማፈላለጊያ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል በማዘጋጀት ያቀርባል፣ የክልሉ ምክር ቤት አባላት፣ ቋሚ ኮሚቴዎችና ሴት ተመራጭ የኮከስ አባላት አቅም በሚገነባበት ሁኔታ እቅድ በማዘጋጀት ተግባራዊ ያደርጋል፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ ያስተባብራል፣ በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶችን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ለመገንባት ለአፈ ጉባኤዎች፣ ቋሚ ኮሚቴዎች፣ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠናዎችን እንዲሁም የአሠልጣኞች ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ ስልጠናዎች ይመራል፤ በየደረጃው የሚሰጡ ስልጠናዎች ያስገኙትን ለውጥ በመገምገም፤ የምክር ቤቶች አሰራር የሚሻሻልበትን መንገድ ይቀይሳል 5. ምክር ቤታዊ አስተምህሮ ሥራዎች ማከናወን • ምክር ቤታዊ የአስምህሮ ሥራዎች የሚመራበት ስትራቴጂና የአሰራር ስርአት በመቀየስ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣ ለምክር ቤታዊ አስተምህሮ የሚያገለግሉ ጥናታዊ ጽሑፎችና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዶች ያዘጋጃል፤ በምክር ቤቶች ታሪክና አሰራር በተመለከተ በሌሎች ባለሙያዎች የተዘጋጁ ሰነዶችን ይገመግማል፤ ግብዓት ይሰጣል፤ በምክር ቤት አስተምህሮ ዙሪያ ጥናት በማካሄድ ለውጡን በመግገምገም ውጤታማ የሆኑ አዳዲስ አሰራሮችን ያመነጫል፣ ይዘረጋል፣ ሂደቱን ያስተባብራል፣ በምክር ቤት አስተምህሮ ሥራዎች ዙሪያ መልካም ተሞክሮችን በመቀመር እንዲሰፉ ያደርጋል፣ በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች የንቅናቄ መድረክ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ሪፖርቶችን በማሰባሰብ የተጠቃለለ ሪፖርት በማዘጋጀት ያቀርባል፣ ከትምህርት ሴክተር ጋር በተደረሰ የጋራ መግባቢያ ስምምነት መሰረት በተመረጡ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ይሰጣል፣ ከሀገር ውስጥ አቻ ምክር ቤቶችና ከውጭ አገር የፓርላማ ልዑካን ወደ ምክር ቤቱ ሲመጡ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ሰለ ምክር ቤቱ አደረጃጀትና አሠራር መግለጫ ይሰጣል፣ ከትምህርት ቤቶችና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ ምክር ቤቱ ለሚመጡ አካላት በምክር ቤቶች ታሪክ፣ አደረጃጀትና አሠራር ዙሪያ ተገቢውን መረጃ ይሰጣል፣ 6. በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ድጋፋዊ ክትትል ማድረግ በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ተግባርና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ማከናወን እንዲችሉ፣ በምክር ቤቶች መካከል የሚስተዋሉ የአፈፃፀም ልዩነቶችን ለማጥበብ የሚረዱ ስትራቴጂዎችን ይቀይሳል፣ በማስፀደቅ ተግባራዊ ያደርጋል፣ በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ድጋፋዊ ክትትል ለማድረግ የሚረዳ ቼክ ሊስት /Check list/ ያዘጋጃል፣ የድጋፋዊ ክትትል ሥራ በበላይነት ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ለድጋፋዊ ክትትል ሥራ አስፈላጊውን የሎጂስቲክ ዝግጅት በማድረግ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፣ በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ድጋፋዊ ክትትል ያደርጋል፣ በጥንካሬና በክፍተት የሚስተዋሉ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችንም በመለየት ግብረ መልስ ይሰጣል፣ የተጠቃለለ የድጋፋዊ ክትትል ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት በማቅረብ ማብራሪያ ይሰጣል፣ 7. የምክር ቤቶች የጋራ ምክክር መድረኮችንና የመወያያ ሰነዶችን ማዘጋጀት ምክር ቤቶች እርስ በርስ ልምድ የሚለዋወጡበት፣ በአሠራር በሚያጋጥማቸው ችግሮች ዙሪያ የሚመክሩነት ውጤታማና ችግር ፈቺ የሆኑ ስትራቴጂያዊ አሠራሮችን በማፍለቅ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤ የጋራ ምክክር መድረኮች በተሳካ ሁኔታ አንዲካሄዱ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ መድረኮችን ያዘጋጃል/ ያስተባብራል በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች አፈፃፀም በመለየት የመወያያ ሰነዶችን ያዘጋጃል፣ ግብዓት በማካተት ያዳብራል፣ የተጠናቀቀ ሰነድ ያቀርባል፣ የጋራ ምክክር መድረኩን ጠቋሚ እቅድ እና የምክር ቤቱን የአፈፃፀም ሪፖርት በማዘጋጀት ያቀርባል የጋራ ምክክር መድረክ አፈፃፀም ሪፖርት ያዘጋጃል፣ የተሰጠ ግብዓት ያካትታል፣ የተጠናቀቀ ሪፖርት ያቀርባል፣ 8. የንቅናቄ መድረኮችንና የመወያያ ሰነዶችን ማዘጋጀት በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ማከናወን እንዲችሉ ክፍተቶችን በመለየት የንቅናቄ መድረክ መወያያ ሰነዶችን ያዘጋጃል፣ የንቅናቄ መድረኮችን ለማካሄድ የሚረዱ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፣ ያስተባብራል ለንቅናቄ መድረክ የሚስፈልግ የበጀት ፕሮፖዛል፣ የማስፈፀሚያ ዕቅድና መርሀ ግብር ያዘጋጃል፣ በማስፀደቅ ተግባራዊ ያደርጋል፣ በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች የንቅናቄ መድረክ አፈፃፀም ይከታተላል፣ ሪፖርቶችን በማሰባሰብ የተጠቃለለ ሪፖርት በማዘጋጀት ያቀርባል፣ አቶ አይነኩሉ ጎሃጽባህ፦ የክትትል፣ ቁጥጥርና ሙያዊ ድጋፍ ዳይረክቶሬት ዳይረክተር