የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች በመንግስት ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎች እና የልማት እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ሁሉንም የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም ለሕብረተሰቡ ወቅታዊና ጥራት ያለውን የመንግስትን ኢንፎርሜሽ ማዘጋጀትና ማሰራጨትእንዲሁም ህብረተሰቡ ያገኘውን መረጃ ተጠቅሞ በልማት እንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፍ ማድረግ፣ መደበኛና አስቸኳይ የምክር ቤት ጉባኤዎችን፤ የምክር ቤቶች የምክክር መድረኮችን፤ የቋሚ ኮሚቴዎች የክትትልና ቁጥጥር ተግባራትን፤ የተለያዩ የመስክ ጉብኝቶችን፤ የህዝብ አስተያየት መስጫ መድረኮችን፣ ልምድ ልውውጦችን እና መሰል ተግባራትንና ክንውኖችን ሁሉንም የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም ለህብረተሰቡ በወቅቱና በጥራት ማዳረስ በምክር ቤቱ የፀደቁ አዋጆች፤ ደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ ህብረተሰቡን የተሟላ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መስራት፣ የክልሉን መልካም ገጽታ የሚያጎለብቱ ፕሮግራሞችን መሥረት በልማትና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ውይይት የፓናል ውይይት መድረክ ማዘጋጀት፣ መክፈቻና መዝጊያ ንግግሮችን ማዘጋጀት፣ የልማት ስራ ጉብኝቶችን ማስተባበር፣ አጫጭር መልዕክቶች፣ መሪ ቃሎችንና ባነሮችን ማዘጋጀት፣ የመስኮት ፎቶ ግራፍ ኤግዚብሽን ማዘጋጀት፣ የሁነት ንግግሮችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት፣ የሕዝብ አስተያየት መሰብሰብ፣ የመንግስትና የህብረተሰብ ቀጥተኛ ግንኙነት ማስተባበር፣ የተለያዩ መድረኮችን የመክፈቻና የመዝጊያ ፕሮግራም ማስተዋወቅ፣ አመታዊና ዜና መጽሄት፣ ካላንደር፣ አጀንዳ፣ ብሮሸርና ቡክሌት እንዲሁም መሰል ተግባራትን በጥራትና በወቅቱ ማዘጋጀት፣ ለሶሻል ሚዲያ፣ ለሬዲዮና ለቴሌቪዥን ዜናና ፕሮግራም ማዘጋጀት፤ አየር ላይ እንዲዉል ማድረግ፣ የሚመለከታቸው አካላት የተለያዩ መግለጫ እንዲሰጡ ያደርጋል፤ በስራ ሂደት ደረጃም መግለጫ እንደየአስፈላጊነቱ ይሰጣል፣ የዞን/ል ወረዳ ፤ ወረዳና የከተማ ምክር ቤቶች የስራ እንቅስቃሴ ይደግፋል ፣ ይከታተላል፣ ምክር ቤቱ ከደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጋር በመሆን የምክር ቤቱን እንቅስቃሴ ለህዝብ ተደራሽ ለሚያደርገው ለሳምንታዊ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራም የሚሆን ዕቅድ ያቅዳል፤ በየደረጃው ካሉ ምክር ቤቶች ግብዓት ያሰባስባል ፤ ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል፣ የለውጥ ስራን ያስተባብራል፡፡