የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዝርዝር ተግባራት

የግብርናዉ ክፍለ ኢኮኖሚ ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ እና የክልሉን በምግብ እህል ራስን የመቻልና የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ አላማ ግቡን እየመታ መሆኑን፤
የክልሉ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃና እንክብካቤ እየተደረገ የአካባቢ ደህንነት ተጠብቆ ለዘላቂ ልማት እየዋለ መሆኑን፤
የአርብቶ አደሩ የኑሮ መሠረት ለሆኑ እንስሳት የጤና አገልግሎት፤ የገበያ መሰረት ልማት፤ የመኖና የዉሃ አቅርቦት እንዲሁም የኤክስቴንሽን ድጋፍ እንዲኖር መደረጉን በአጠቃላይ ክልሉ ለአርብቶ አደሮች የሚያደርገዉን ልዩ ድጋፍ አፈጻጸም መከታተልና መቆጣጠር፤
ሕጎችና ዕቅዶች ሲወጡ የአርብቶ አደሩን ጥቅም ያገናዘቡ መሆናቸዉን፣ በአርብቶ አደሩ ዉስጥ ፈጣን ልማት በማምጣት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሕይወቱ እየተለወጠ መሆኑን፤
በአርብቶ አደሩ አካባቢ የሚታቀዱ በመንደር የማሰባሰብ ፕሮግራሞች በአርብቶ አደሩ ፈቀደኝነት ላይ የተመሰረቱ መሆናቸዉን እንዲሁም በአርብቶ አደሩ አከባቢ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሚወገዱበትን ሁኔታ መመቻቸቱንና ተግባራዊነቱን መከታተልና መቆጣጠር፤
አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ላመረተዉ ምርት ተመጣጠኝ ዋጋ የሚያገኝበት ሁኔታ መመቻቸቱን፤
የዉሃ ማዕድንና የኢነርጂ ልማት አጠቃቀም፤ ተደራሽነትንና ፍትሐዊነትን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ሌሎች በኮሚቴዉ ሥር የተደለደሉ መስሪያ ቤቶች አላማና ተልዕኮ መሰረት በማድረግ አስፈላጊዉን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፡፡ የአፈጻጸም ሪፖርትም ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡

ግብርናና ገጠር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በስሩ የሚከታተላቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች

የግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ፣
የማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ፣
ደንና አካባቢ ጥበቃ ቢሮ፣
የክልሉ የአርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ ናቸው፡፡