የበጀት፣ ፋይናንስና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የበጀት ፋይናንስና ኦዲት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዝርዝር ተግባራት በምክር ቤቱ ለክልሉ መንግስት የተመደበ ማንኛዉም በጀት በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤ ኮሚቴዉ የዋና ኦዲተር ሪፖርትን ይመረምራል፤ በሚመረምርበት ወቅትም የተመደበዉ በጀት ለታለመለት ዓላማና አገልግሎት ወጪ የተደረገ መሆኑን፤ ወጪዉ ስልጣን ባለዉ አካል የተረጋገጠ መሆኑን፤ የበጀት ዝዉዉር ሲኖር በፋይናንስ ህጉ መሰረት መከናወኑን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤ በምክር ቤቱ ትዕዛዝ በዋና ኦዲት መስሪያ ቤት የተከናወነ የንብረት ኦዲት ዉጤትን ይገመግማል፤ በማንኛዉም መንግስታዊ አካል በበጀት ዓመቱ ከተመደበዉ በላይ የበጀት አጠቃቀም ሲኖር ኮሚቴዉ ከበጀት በላይ ለማዉጣት አስገዳጅ የሆነዉን ምክንያት የማጣራትና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘውም ሪፖርትና የዉሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ የማቅረብ ሀላፍነት አለበት፤ ከኮሚቴዉ ተግባር ጋር ተያያዥነት ያላቸዉን የክልሉን ፖሊሲዎች፣ ሕጎች፤ስትራቴጂዎች፤ ፕሮግራሞችና ዕቅዶች በአግባቡ በስራ ላይ መዋላቸዉን ይቆጣጠራል፤ ይከታተላል፡፡ የክልሉ መንግስት ዓመታዊና ተጫማሪበጀት በአግባቡ መጽደቁንና ስራ ላይ መዋሉን፤ የክልሉ መንግስት ገንዘብና ንብረት በአግባቡ መሰብሰቡን እና መጠበቁን ፤ ለክልሉ ከፌዴራል የሚሰጡ ድጎማዎችና ክልሉ ለዞንና ልዩ ወረዳ የሚሰጠዉ የበጀት ድጎማ በቀመሩ መሰረት መሆኑን ይከታተላል፡፡ የአፈጻጸም ሪፖርትም ለምክር ቤቱ ያቀርባል::