የሕግ፤ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የሕግ፤ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዝርዝር ተግባራት

 • የክልሉን መንግስት የፍትህና አስተዳደራዊ አሰራሮች ህገ-መንግስቱን መሰረት በማድረግ መደራጀታቸዉንና መፈጸማቸዉን መከታተልና መቆጣጠር፤
 • በህገ -መንግስቱ የተደነገጉ መብቶችና ነጻነቶች በአግባቡ መተግበራቸዉን መከታተልና መቆጣጠር፤
 • ህብረተሰቡ ነጻ፤ፍትሃዊና ቀልጠፋ የፍትህ አገልግሎት ማግኘቱን፤
 • ሙስናና ብልሹ አሰራርን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል ስርአት በአግባቡ መደራጀቱን መከታተልና መቆጣጠር፤
 • የፍትህና የአስተዳደር ፖሊሲዎች፤ ህጎች፤ ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች በአግባቡ በስራ ለይ መዋላቸዉን መከታተልና መቆጣጠር፤
 • አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ምክር ቤቱ ወደማንኛዉም ቋሚ ኮሚቴ የሚመረዉን ረቂቅ ህጎች እና ስምምነቶች የህግ ይዘቱን መመርመር፤
 • በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 49/2/ለ/ የተመለከተዉን የሕግ ከለላ የማንሣት እንደዚሁም ሌሎች የአባላት መብትና ስነ ምግባር ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ይመረምራል፡፡ የአፈጻጸም ሪፖርትም ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡

የህግ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በስሩ የሚከታተላቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች

 • ፍትህ ቢሮ
 • ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
 • ጠቅላይ ፍ/ቤት
 • ፖሊስ ኮሚሽን
 • ስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን
 • ማረሚያ ተቋም
 • ር/መስተዳድር ጽ/ቤት
 • ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት
 • ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ
 • ሚሊሻ ጽ/ቤት
 • የፍትህ አካላት ባለሙያዎች ስልጠና ማዕከል