ስልጣንና ተግባር

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ስልጣንና ተግባር

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት በክልሉ እየተካሄደ ያለውን የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ግንባታ ሂደት በማፋጠን ህዝቡ ከድህነት ተላቆ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል ከተፈጠሩ ህገ መንግስታዊ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ህገ መንግስት ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ምክር ቤቱ በተሻሻለው የ1994 ዓ.ም የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሕገ መንግሥት አንቀጽ 51 በተሰጠው ስልጣን መሰረት፡-

 • ሕግ አውጪ አካል ነው፣
 • ሕገ መንግሥትና ሌሎች ሕጎችን የማይፃረሩ ልዩ ልዩ ሕጎችን ያወጣል፣
 • ብዛት፣ የአካባቢውን ስፋትና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ግምት ውስጥ በማስገባት በክልሉ ውስጥ ተጨማሪ የአስተዳደር እርከኖችን ወይም የራስ በራስ አስተዳደራዊ አካባቢዎችን ያቋቁማል፣
 • መንግሥት ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ከአጎራባች ክልል መንግሥት ጋር የሚደረገውን ስምምነት ያፀድቃል፣
 • ቤቱ አባላት መካከል ርዕሰ መስተዳድሩን ይመርጣል፤ በርዕሰ መስተዳድሩ አቅራቢነት የክልል መስተዳድር ምክር ቤት አባላትን ሹመት ያፀድቃል፣
 • የቁጥጥር አካሉን ያቋቁማል፣
 • ምሕረት ያደርጋል፣
 • ሠላምና ፀጥታ ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ያወጣል፤ የፀጥታና የፖሊስ ኃይሉን ያቋቁማል፣
 • ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኘሮግራሞች ያፀድቃል፣
 • የገቢ ምንጮች የሚመለከቱ ሕጎችን ያወጣል፤ የክልሉን መንግሥት በጀት ያፀድቃል፣
 • አገልግሎት መስፋፋትና ለኢኮኖሚያዊ ልማት መፋጠን አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን ያቋቁማል፣
 • ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት፣ ምክትል ኘሬዝዳንት፣ ዋና ኦዲተርና ምክትል ዋና ኦዲተሩን ይሾማል፣
 • መንግሥት በተከለለው የገቢ ምንጭ በክልሉ ውስጥ ግብርና ታክስ ይጥላል፣
 • የሠራተኛ አስተዳደርና የሥራ ሁኔታዎችን በተመለከተ ሕግ ያወጣል፣
 • ጊዜ አዋጅ ያፀድቃል፣
 • ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች የክልሉን መንግሥት ባለሥልጣናት ለጥያቄ ይጠራል፤ የአስፈጻሚውን አካል አሠራርም ይመረምራል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት በ2017 ዓ.ም የሕዝብ ሥልጣን ባለቤትነት የዳበረበት የመልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ ተምሳሌት ሆኖ የማየት ራዕይ ሰንቆ የምክር ቤቱን አሰራር በማሻሻል በኅብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ለክልሉ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መፋጠን ፋይዳ ያላቸውን ሕጎች በማውጣት፣ አፈፃፀማቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር ቁርጠኛ የመንግስት አካላትን በማደራጀት የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት እንዲረጋገጥ፣ የግልፀኝነትና ተጠያቂነት አሠራር ዕውን እንዲሆን እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲዳብር የማድረግ ተልዕኮ ይዞ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ እስከ አሁን ባከናወናቸው ህገ መንግስታዊ ተግባራትም በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች የማይናቅ የዕድገት ለውጥ ተመዝግቧል፡፡