ደንብ ቁጥር 133/2008 የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለማቋቋም የወጣ ደንብ

የክልሉን የኢኮኖሚ ልማት ለማፋጠንና የክልሉን ኑዋሪዎች የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ኢንቨስትመንትን ማበረታታትና ማስፋፋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ የክልሉን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማሳደግ፣ ለማስፋፋት እና በአግባቡ ለመምራት ዘርፉን  በበላይነት የሚያስተዳድሩትን አካላት በመወሰን ተግባርና ሃላፊነታቸውን በግልጽ መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት መስተዳደር ምክር ቤት የክልሉን