የጉባኤ ጥሪ

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከመጋቢት 7-11/2014 ዓ.ም ድረስ በክልሉ ምክር ቤት የጉባኤ አዳራሽ ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም የክልል ምክር ቤት አባላት መጋቢት 7 ቀን 2014 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በክልሉ ምክር ቤት ጽ/ቤት በአካል ተገኝታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉና ጉባኤው የሚወያይባቸውን ሰነዶች እንድትወስዱ እናስታውቃለን፡፡
       የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት