የደቡብ ክልል የፌዴራል ተወካዮች ከመረጣቸው ከህዝብ የተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ

እየቀረበ ባለው የደቡብ ክልል የፌዴራል ተወካዮች ከመረጣቸው ህዝብ የተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መካከል የወረዳ፣ የልዩ ወረዳ፣ የዞንና የክልል እንሁን የመዋቅር ጥያቄዎች ይገኙበታል። ከዚህም ባለፈ በከተሞች አካባቢ የመሬት ወረራ መበራከት፣ የፀጥታ ሰጋት፣ በፍርድ ቤቶች አካባቢ የፍትህ መጓደል፣ ኢፍትሃዊ የሆነ የመሠረተ ልማት ተደራሽነት በዘላቂነት ልፈታ ይገባል ብለዋል ተመራጮቹ። ሌብነት፣ ብልሹ አሰራር፣ የኦዲት ቁጥጥር ልልነትና ተጠያቂነት ያለመኖር፣ አመራሩ በዝምድናና በልዩ ልዩ ኔትወርክ መጠላለፍ፣ የአመራር ብቃት ችግር ህዝቡ በስፋት ያነሳቸው ናቸው። ክልሉ ከሌሎች ክልሎችና ጎሮቤት ሀገር ኬንያ ጋር በሚያዋስንባቸው አካባቢዎች የሚከሰተውን የፀጥታ ችግር ክልሉ ከፌዴራልና ከአጎራባች ክልሎች ጋር በመቀናጀት መፍታት እንዳለበትም ተነስቷል።