የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዝርዝር ተግባራት

 • ፈጣን ልማት ለማምጣትና በዴሞክራሲ የታነጸ ህብረተሰብ ለመፍጠር በብቃት፣በጥራት፣ በታማኝነትና በቁርጠኝነት ሊሰራ የሚችል የሰለጠና የሰዉ ኃይል በአጭር ጊዜና በሰፊዉ ለማፍራት የሚደረገዉን እንቅስቃሴ መከታተልና መቆጣጠር፤
 • የክልሉን አጠቃላይ የማህበራዊ ልማት፤ የትምህርት፤ የጤና፤ የፕሬስ፤ የባህል የአቅም ግንባታ እና ሌሎች ፖሊሲዎች፣ህጎች፣ ስትራቴጂዎች እና ዕቅዶች በአግባቡ በስራ ለይ መዋሉን ይመራምራል፤ይቆጣጠራል፤
 • ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች ተጠብቀዉ ለትዉልድ የሚተላለፍበት መንገድ መቀየሱንና ተግባራዊ መሆኑን መከታተልና መቆጣጠር፤
 • የመገናኛ   ብዙሃን ለክልሉ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት- ግንባታ ሠላም ልማትና መልካም አስተዳደር የበኩላቸዉን ሚና እየተጫወቱ መሆናቸዉን እና የብዙሃን መገናኛ ቦርድም የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣቱን መከታተል፤
 • ለክልሉ የቱሪዝም ምንጭነት የሚያገለግሉ አስፈላጊ ሁኔታዎች መመቻቸታቸዉን መከታተል፤
 • የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት የሚረዱ እንቅስቃሴዎችን መከታተልና መቆጣጠር፤
 • የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎቶችን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች፤ የአረጋዉያን፤ የአካል ጉዳተኞች፣ ሥራ አጥነትና ሌሎች የማህበራዊ ነክ ጉዳዮች አፈጻጸምን መከታተልና መቆጣጠር፤
 • ሌሎች በኮሚቴዉ ስር የተደለደሉ መስሪያ ቤቶች ዓላማና ተልዕኮዉን መሰረት በማድረግ አስፈላጊዉን የክትትልና የቁጥጥር ሥራ ያከናዉናል፡፡ የአፈጻጸም ሪፖርትም  ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡
 • በህገ መንግስቱ የተደነገጉትን የሴቶች መብት መከበራቸዉና በመብቶቻቸዉ ተጠቃሚ መሆናቸዉን መከታተል፤
 • ህጻናትንና ወጣቶችን የሚጨቁኑ ህጎች መመርመርና እንዲሻሻሉ ማድረግ፤አዳዲስ የህግ ሃስቦችን ማመንጨት፤
 • እቅዶች ሲወጡና ሲጸድቁ የጾታ አድሎን ያስወገዱና ስርአተ ጾታን ያገናዘቡ መሆናቸዉን ማረጋገጥ፤
 • በኢኮኖሚና በማህበራዊ መስኮች እንዲሁም በመንግስትና በግል ተቋማት ሴቶች ከወንዶች እኩል ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታያታቸዉ የደረሰባቸዉን የታሪክ ጠባሳ ማረም የሚያስችሉ ልዩ የድጋፍ እርምጃ ተጠቃሚ የሚሆኑበት መንገድ ማመቻቸት፤
 • ንብረት የማፍራት፤ የማስተዳደርና የመቆጣጠር፤ የመጠቀም የማስተላለፍና የማዉረስ መብቶቻቸዉ መከበሩን መከታተልና መቆጣጠር፤
 • በቅጥር፤ በስራ ዕድገት የእኩል ክፊያና ጡረታ ለማስተላለፍ ያላቸዉን የእኩልነት መብት መረጋገጡን መከታተልና መቆጣጠር፣
 • ወጣቶች ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ተጽዕኖ ለማላቀቅ ሴቶችን የሚጨቁኑ በአካላቸዉ ወይም በአእምሯቸዉ ላይ ጉዳት የሚያደርሱትን ህጎች፤ወጎችና ልምዶችን መከላከልና መቆጣጠር፤
 • በእርግዝናና በወሊድ ምክንያት የሚደርስባቸዉን ጉዳት መከላከልና ጤንነታቸዉን ለማስጠበቅ የሚያስችል የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርት መረጃ አቅም የማግኘት መብትን መከታተልና መቆጣጠር፤
 • ወጣቶች በጥያቄዎቻቸዉ ዙሪያ እንደ ፍላጎታቸዉና እንደ ችግራቸዉ ዓይነት ተደራጅተዉ ችግሮቻቸዉን ለማስወገድ እንዲታገሉ መብታቸዉን እንዲያስከብሩ ድጋፍ መስጠት፤
 • የክልሉ መንግስት የሚያደርገዉ እንቅስቃሴ የሴቶችን እኩል ተሳታፊነታቸዉንና ተጠቃሚነታቸዉን ያረጋገጠ እንዲሆን ለማስቻል በህገ- መንግስቱ በህግና በሴክተር ፖሊሲዎች መሰረት መከናወኑን መከታተልና መቆጣጠር፤
 • ስፖርት ፖሊሲዎች፣ ሕጎች፣ ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች በአግባቡ በሥራ ላይ መዋላቸዉን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
 • መንግስቱ የተረጋገጡ መብቶች መከበራቸዉን፣ ሕጻናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰዱበት ጊዜ በመንግስታዊ ወይም በግል የበጎ አድራጎት ተቋሞች፤ በፍርድ ቤቶች የህጻናት ደህንነት በቀደምትነት መታሰባቸዉን እና የህጻናት ደህንነታቸዉንና ትምህርታቸዉን የሚያራምዱ ተቋሞች መመስረታቸዉን ይከታተላል፤ ይቆጣጠረል፡፡ የአፈጻጸም ሪፖርትም ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡

 

የሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በስሩ የሚከታተላቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች፣

 1. ጤና ቢሮ
 2. ትምህርት ቢሮ
 3. ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ
 4. የባህልና ቱሪዝም ቢሮ
 5. የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
 6. የሴቶችና ህፃናት ቢሮ
 7. የፐቢሊክ ሰርቪሲና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ
 8. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ
 9. የደቡብ አመራር አካዳሚ
 10. የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
 11. የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ
 12. ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት   ናቸው፡፡