የህዝባችንን አንገብጋቢ የሆኑ የከተማ መሬትና መሬት ነክ ጥያቄዎችን ለመመለስ በህግና መመሪያ በአሰራር ለመፍታት እየተሰራ ነው

የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድርና የከተማና ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ ተከበሩ አቶ ተስፋዬ ይገዙ ኑሮ ውድነትን በተመለከተም የአቅርቦትና ፍላጎት ያለመመጣጠን መከሰቱን ጠቁመው መንግስትና ህዝባችን በቅንጅት በመስራት እየተፈታ የሚሄድ እንደሆነ አንስተው ህገ ወጥ ንግድ ላይ በመዝመት፣ አቅርቦትን ከፍ ማድረግ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው። ከስራ አጥነት አንጻር የተሰሩ ሥራዎች ቢኖሩም ከፍላጎት፣ ከጥራትና ከውጤታማነት አንጻር ቀሪ ነገሮች ስላሉ በርትቶ መስራት ይጠይቃል ብለዋል።በክል ሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የፀጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ መንግስት ከፍተኛ ሀብትና የሰው ኃይል መድቦ እየሰራ መሆኑን የጠቆሙት የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ለውጤታማነቱም የሁሉንም ቀና ትብብር ይጠይቃል በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች እየተነሳ የሚገኘው የክልል መዋቅር ጥያቄ በከፍተኛ የኃላፊነትና በጥንቃቄ የሚመራ በመሆኑ ከህዝባችን ጋር በግልጽና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በመወያየት እልባት የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል። የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በፌዴራል ፓርላማ የመንግስት ዋና ተጠሪ እንዳነሱት ከመራጩ ህዝብ የተነሱ ልዩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ችግራቸው ተለይቶ የመፍትሄ አቅጣጫ መስጠት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ብለዋል።በተደጋ ሚ ህዝቡን ማዳመጥ እንዳለብን ተነጋግረናል፤ በዚህ ልክ አመራሩ ህዝብን ማዳመጥ፣ አዳምጦ ችግሩን መተንተንና የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ ከዚያም መተግበርና ለህዝቡም ማሳወቅ አለብን ብለዋል። በማጠቃለያም የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ ከህዝባችን የተነሱ ጥያቄዎች በተለያዩ ጊዜያት የተነሱና አቅጣጫም የተቀመጠላቸው በመሆኑ ፈጥኖ ወደ ተግባር መግባትን ይጠይቃል ብለዋል።ለተግባራዊነቱም ምክር  ቤቱ ከክትትልና ቁጥጥር ባለፈ የቅርብ ድጋፍ እንደሚያደርግም ክብርት አፈ ጉባኤዋ ገልጸው የተነሱ ጥያቄዎች በየደረጃው እየተፈተሹ የሚፈቱ ይሆናል በማለት ውይይቱን አጠቃለዋል።