የሀረሪ ህዝብ ክልል ምክር ቤት

ሚያዚያ 3/2014 የሀረሪ ህዝብ ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮች ከደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት ማኔጅሜንት አባላት ጋር የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።

የሀረሪ ህዝብ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ የለውጥ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን አመራሮቹ አንስተው የልምድ ልውውጡ ዓላማም በምክር ቤቱ አደረጃጀት፣ አሰራር ዙሪያ ልምድ በመቀመር ተግባራዊ ለማድረግ እንደሆነ አንስተወል። የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት ማኔጅሜንት አባላትም በቼክ ሊስት በቀረበው ጥያቄ መሠረት ምላሽ የሰጡ ሲሆን የሀረሪ ህዝብ ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮችም ለስራቸው አጋዥ የሆነ ልምድ ልውውጥ እንዳደረጉ በመግለጽ ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል አመስግነዋል።